Ladda ner PDF
Tillbaka till listan med berättelser

ለትክክለኛው ምክንያት መቆም

Skriven av LIDA Portugal

Illustrerad av Sunniva Høiby-Øiset

Översatt av Loza Tadesse Mamo

Uppläst av Dawit Leykun

Språk amhariska

Nivå Nivå 4

Läs hela berättelsen

Reading speed

Automatisk avspälning


ኤድሰን የተወለደው ሀገሪቱ ነፃ ከወጣች በኋላ በአንጎላ ነበር። በጣም ረጅም ልጅ ነበር። ከቁመቱ የተነሳ ጎልቶ ወጣ። በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ህፃናት ወታደር ሆነው እንዲዋጉ መሳሪያ እየሰጡ የነበሩ ሰዎች እንደ እሱ ያሉ ወንዶች ልጆችን ይፈልጋሉ።


እናቱ እንዳይወስዱት ስለፈራች ከአክስቱ ጋር ወደ ፖርቹጋል እንዲኖር ልትልከው ወሰነች። እዚያ ደህና እንደሚሆን አሰበች።


ኤድሰን ሞቃታማውን የአየር ጠባይ፣ ባህላዊ ምግብ እና ከሁሉም በላይ የእናቱን እቅፍ እና መሳም ስለሚናፍቀው ኑሮውን ለመጀመር በጣም ከባድ ነበር።


ፖርቱጋልኛ በደንብ አልተናገረም እና ትምህርቶቹን እና የክፍል ጓደኞቹን ንግግሮች ለመከታተል በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘው። በስተመጨረሻ ወደ ፖርቱጋል መምጣቱ ከጅምሩም ጥሩ ይሁን አይሁን ሀሳብ ገባው።


አንድ ቀን አንድ አስተማሪ በቅርጫት ኳስ ጎበዝ መሆኑን አስተዋለ። የቅርጫት ኳስ ቡድንን ተቀላቀለ እና በጣም ስኬታማ ነበር። በትምህርት ቤት ታዋቂ ሆነ እና ጓደኞች አፍርቷል። እሱ ደግሞ የበለጠ በራሱ የሚተማመን ሆነ።


አሁን ጎልማሳ በመሆኑ ኤድሰን ከህብረተሰቡ የመገለል አደጋ ላይ ያሉ ልጆችን እና ሌሎችን ያሰለጥናል። አንድ ጊዜ ቁመቱ የልጅ ወታደር የመሆን አደጋ ላይ ጥሎት ነበር። አሁን ግን ቁመቱ ሌሎች ደህንነት እንዲሰማቸው ለመርዳት ጥንካሬ ይሰጠዋል።


Skriven av: LIDA Portugal
Illustrerad av: Sunniva Høiby-Øiset
Översatt av: Loza Tadesse Mamo
Uppläst av: Dawit Leykun
Språk: amhariska
Nivå: Nivå 4
Creative Commons Licens
Detta verk är licensierat under en Creative Commons Erkännande 4.0 Internationell Licens.
Valmöjligheter
Tillbaka till listan med berättelser Ladda ner PDF